የነጻነት ጥያቄን እንደ ግል ጥል እንጂ እንደመብት ፍለጋ የማያየው ያገራችን እንደልቡ የሆነ ነጻነትን አፋኝ መንግስት ዛሬም የፍለገውን ወይም የፈቀደዉን ሲዘጋና ሲከፍት ሲያስር እና ሲፈታ እንዲሁም እውነታውን የሚያጋልጡ ነጻ ፕሬሶችን ሲያግድ እናያለን ።
ለህግ እና ደንብ ተገዥ ያልሆነ መንግስት፣ህግ የማይጠይቀው፡ ገለልተኛ አካል በሌለበት ግለሰብን እና ሚዲያን ህግ እና ደንብን አላከበራችሁም በሚል የሀሰት ክስ እንደገዛ ፍቃዱ እያሰረ እና እየዘጋ ይገኛል ፣ ከነዚህም ውስጥ አንዱ የፍትህ ጋዜጣ እንዲሁም በቅርቡ የታገደው በየ 2 ሳምንቱ 35 ሺህ ቅጂ ይታተም የነበረው አዲስ ታይምስ መፅሄት ነው።
መጽሄቱ ተነባቢነቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ከአስር ሽ ተነስቶ ሰላሳምስት ሽ ፔጀች መድረሱን ዳይሬክተሩ ተመስገን ደሳለኝ ገልጹዋል።
ለመታገዱ በምክንያትነት ከተገለጸው ውስጥ ሸሩ ከቀድሞ ባለቤቱ ወደ አዲስ ባለቤቶች ሲዞር በ15 ቀን ውስጥ አላሳወቃችሁም፡ እንዲሁም ሚዲያው እየተንቀሳቀሰ ያለው በባለቤቶቹ ፋይናንስ አይደለም የሚል ይገኝበታል።ምክንያቶቹ ያው የተለመደው የሀሰት ክስ እና ማስረጃ አልባ ውሳኔ ሲሆን፡ እውነታ ነው ተብሎ ቢገመት እንኩዋን ወንጀል እንደመሆኑ መጠን ባለቤቶቹ በህግ ሊጠየቈ ሲገባ ህትመቱ እንዲቆም ብቻ ነው የተደረገው። በተጨማሪም ባለቤቶቹ የሀስት ውንጀላ ለመሆኑ እና መጽሄቱን ለማሳተም አስፈላጊውን ደንብ እንደፈጸሙ በቂ ማስረጃ በጃቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል። ያም ሆኖ ተከሳሽ ማን ? ህግ አስፈጻሚ ማን?
በተጨማሪ የሙስሊም ጉዳይ የተባለ ሀይማኖታዊ ጋዜጣ ኤዲተር ሰለሞን ከበደ ታስሮል።
ኢትዩጲያ በአለም አቀፍ የፕሬስ ነጻነት የሰብአዊ መብት ተቈዋማት በፕሬስ አፍኝነቱዎ ትታወቃለች ፡ ይህም ሆኖ በየግዜው አገር እና ህዝብ ወዳድ የሆኑ ፡የመንግስትን አፈና እና እስር እየተቀበሉ፡ዋጋ እየከፈሉ ለአመኑበት እውነት የቆሙ አንዳንዶች አይታጡም።
No comments:
Post a Comment