Friday, 14 June 2013

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከዓመት ከስድስት ወር እስር በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሊቲ ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው ተፈቀደ


ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ለሚያሰሙ ምስጋና አቅርቧል
"ስላደረጋችኹልኝ እና ስለምታደርጉልኝ ኹሉ አመሰግናለሁ!" እስክንድር ነጋ
"እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ፤ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ" ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ Jornalist Eskinder Nega
                                        (ዓርብ ሰኔ 7 ቀን 2005 ዓ.ም. June 14, 2013)
 ላለፉት አስራ ስምንት ወራት በእስር ላይ ያለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከባለቤቱ ከጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ከናፍቆት ሌላ ሰው እንዲጠይቀው በዚህ ሣምንት መፈቀዱን ለመረዳት ችለናል። ዛሬ ጠዋት ቃሊቲ ሄደው ከጠየቁት ውስጥ ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ አንዷ ስትሆን፤ አላግባብ ከሕግ ውጪ መታሰሩን ተረድተው በያሉበት ድምፃቸውን ላሰሙና ለሚያሰሙ ሁሉ በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው ብሏታል።


ካላግባብ፣ ከሕግና ከሰብዓዊ መብት ውጭ ጋዜጠኛ እስክንድር ከልጁና ከባለቤቱ በስተቀር ማንም ወዳጅ ዘመድ እንዳይጠይቀው መደረጉ በገዥው ፓርቲ የፖለቲካ አመራሮች ግለሰባዊ ትዕዛዝ እንደነበር ብዙዎች ሲተቹት እንደነበር ይታወቃል። ከዚህም ሌላ የምዕራባውያን ሀገሮች ባለሥልጣናትና መንግሥታት ካላግባብ እንደ እስክንድር በእስር ላይ ያሉት ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱ እየጎተጎቱ ይገኛሉ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ጋር በነበረው ቆይታ እንዲህ ሲል ምስጋና አቅርቧል፤ "የታሠርኩት ከሕግ ውጭ መኾኑን ተረድታችሁ በሁሉም መንገድ እንድፈታ ለወተወታችሁ፣ ላሳሰባችሁ፣ አሁንም እየወተወታችኹ ላላችኹና ባላችኹበት ላሰባችኹኝ ኹሉ ዲሞክራሲ በአገራችን ሰፍኖ ከእስር ወጥቼ በአካል ምስጋናዬን እስካቀርብላችሁ ድረስ ባላችሁበት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ!"።

ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ ዛሬ በፌስ ቡክ ገጿ ላይ "እስክንድር ነጋን አገኘሁት!" በሚል ርዕስ ባስነበበችው ማስታወሻዋ ላይ ከጋዜጠኛ እስክንድር ጋር በነበራት ቆይታ፣ ስለጋዜጠኛው ያላትን አመለካከት እንዲሁም ስለሁኔታው አስመልክታ እንዲህ ስትል አስነብባለች፦

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቃሊቲ የሚገኘው እስር ቤት ከገባ ከዐሥራ ስምንት ወራት በላይ አስቆጥሯል። ለዚህን ያህል ጊዜም ከባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል እና ከልጁ ናፍቆት በስተቀር አንድም ሰው ገብቶ እንዲጠይቀው አልተፈቀደለትም ወይም በወዳጅ ዘመዶቹ የመጠየቅ መብቱ ተነፍጎ ነበር። ከቀናት በፊት ግን ይህ መብቱ ተከብሮለት ሰዎች ገብተው እንዲጠይቁት መፈቀዱን ሰማኹና ዛሬ ጠዋት እስክንድርን ለማየት ወደ ቃሊቲ አመራሁ። እስክንድርንም አገኘኹት ብዙም ተጨዋወትን። እስክንድር ለዚህን ያህል ወራት እስር ቤት መቆየቱን ተጠራጠርኩ ጥንካሬው አሁንም አብሮት አለ።

ከእርሱ ይልቅ እርሱን ያሳሰበው በውጭ ያሉት ወዳጆቹ ጤንነት እስኪመስለኝ ድረስ በጋራ የምናውቃቸውን ሰዎች እና ጓደኞቻችንን ስም እያነሳ ጠየቀኝ። በቻልኩት መጠን ሰላምታ እንዳቀርብለትም አሳሰበኝ። በመጨረሻም እንዲህ አለኝ፤ "የታሠርኩት ከሕግ ውጭ መኾኑን ተረድታችሁ በሁሉም መንገድ እንድፈታ ለወተወታችሁ፣ ላሳሰባችሁ፣ አሁንም እየወተወታችኹ ላላችኹና ባላችኹበት ላሰባችኹኝ ኹሉ ዲሞክራሲ በአገራችን ሰፍኖ ከእስር ወጥቼ በአካል ምስጋናዬን እስካቀርብላችሁ ድረስ ባላችሁበት የከበረ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ!" መልዕክቱን በፌስቡክ ገጼ ላይ እንደማሰፍርለት ቃል ገብቼለት ተሰናብቼው ወጣሁ። በገባሁት ቃል መሠረትም ምስጋናውን አድርሻለኹ።

እስክንድር ነጋ የሞያ አጋሬ ብቻ አይደለም፤ በቀናነታቸው እና በአስተዋይነታቸው የመጀመሪያውን የወዳጅነት ቦታ ከምሰጣቸው ጓደኞቼ ውስጥ የምመድበው ሰው ነው። እስክንድር በአሳሪዎቹ እጅ ወድቆም ስለ ሌሎች ማሰብ ባለማቋረጡ እየተገረምኩ ቃሊቲን ለቅቄ ወጣሁ። ወዳጆቼ በዚህ ቤት መታሠር ሚያቆሙት መቼ ይኾን ስልም ራሴን ጠየኹ!
ምንጭ᎓ ኢትዮጲያ ዛሬ

ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም


ጦርነት 
እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩሞ ልተውነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለወይየአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግና እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡


ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስምነበር ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ —
1. የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤በዓየርኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛነው፤
2. በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁማኅበር ታዛቢ አባልነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤ በዚህ ሁሉመሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን ነች፤
3. የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤
ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤ ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ›› ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼታስሬአለሁ፤ ስለዚህ አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው፡፡

ምንጭ᎓ ኢትዮጲያ ዛሬ

Monday, 10 June 2013

Ginbot 7 Spokesperson, Ato Efrem Madebo, on the G7 4th Quarter Conference .

Ginbot 7 Movement for Justice freedom and Democracy, Foreign  Affairs Ephrem Madebo's Interview on ESAT Satellite Television about the 4th  Quarter G7 Meeting.