Saturday, 25 May 2013

Today 25 may 2013 ,a number of People from Ethiopia who lives in Harstad Norway,demonstrate protest against the dictatorship regime in Ethiopia.

The Ethiopian regime is one of the worst dictatorships ever in the country’s history. Ethiopian citizens have no freedom of speech and their is no free press. Many  journalists are in prison today than it was in the past. The government uses Anti-terrorism law to eliminate the opposition by convicting the innocent people and  also Corruption is characteristic of this regime.
 Government chases people out of their land and sell to Chinese, Indian or Arab Saud companies. Government export agricultural products to acquire weapons while millions of citizens affected by famine.
 Government violates basic human rights.
 It is neither a Democratic or a fair system in the country. The regime practice  systematic discrimination.
 Today we demonstrate and demand democracy, human rights and justice for all ,says one of the protester.And the slogans they were holding was: 
 • Political prisoners must be released now!
 • Prisoners of conscience must be released now!
 • Journalists must be released now!
 • We never accept discrimination
 • Norway should not fund the dictatorship in Ethiopia
 • We need solidarity from the Norwegian people!

http://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=pkpTTw4sXX4

http://www.ht.no/incoming/article7623937.ece#.UaEUTdZqf_w.facebook


Friday, 24 May 2013

Amnesty International 2013 Annual Report: Ethiopia


  • Background
  • Freedom of expression
  • Human rights defenders Torture and other ill-treatment
  • Arbitrary arrests and detentions
  • Excessive use of force
  • Conflict in the Somali region
  • Forced evictions

    The state stifled freedom of expression, severely restricting the activities of the independent media, political opposition parties and human rights organizations. Dissent was not tolerated in any sphere. The authorities imprisoned actual and perceived opponents of the government. Peaceful protests were suppressed. Arbitrary arrests and detention were common, and torture and other ill-treatment in detention centres were rife. Forced evictions were reported on a vast scale around the country.
    Background
    In August, the authorities announced the death of Prime Minister Zenawi, who had ruled Ethiopia for 21 years. Hailemariam Desalegn was appointed as his successor, and three deputy prime ministers were appointed to include representation of all ethnic-based parties in the ruling coalition.Amnesty International 2013 Report: Ethiopia
    The government continued to offer large tracts of land for lease to foreign investors. Often this coincided with the “villagization” programme of resettling hundreds of thousands of people. Both actions were frequently accompanied by numerous allegations of large-scale forced evictions.
    Skirmishes continued to take place between the Ethiopian army and armed rebel groups in several parts of the country – including the Somali, Oromia and Afar regions.
    Ethiopian forces continued to conduct military operations in Somalia. There were reports of extrajudicial executions, arbitrary detention, and torture and other ill-treatment carried out by Ethiopian troops and militias allied to the Somali government.
    In March, Ethiopian forces made two incursions into Eritrea, later reporting that they had attacked camps where they claimed Ethiopian rebel groups trained (see Eritrea entry). Ethiopia blamed Eritrea for backing a rebel group that attacked European tourists in the Afar region in January.
    Freedom of expression
    A number of journalists and political opposition members were sentenced to lengthy prison terms on terrorism charges for calling for reform, criticizing the government, or for links with peaceful protest movements. Much of the evidence used against these individuals consisted of examples of them exercising their rights to freedom of expression and association.
    The trials were marred by serious irregularities, including a failure to investigate allegations of torture; denial of, or restrictions on, access to legal counsel; and use of confessions extracted under coercion as admissible evidence.
    • In January, journalists Reyot Alemu, Woubshet Taye and Elias Kifle, opposition party leader Zerihun Gebre-Egziabher, and former opposition supporter Hirut Kifle, were convicted of terrorism offences.
    • In June, journalist Eskinder Nega, opposition leader Andualem Arage, and other dissidents, were given prison sentences ranging from eight years to life in prison on terrorism charges.
    • In December, opposition leaders Bekele Gerba and Olbana Lelisa were sentenced to eight and 13 years’ imprisonment respectively, for “provocation of crimes against the state”.
    Between July and November, hundreds of Muslims were arrested during a series of protests against alleged government restrictions on freedom of religion, across the country. While many of those arrested were subsequently released, large numbers remained in detention at the end of the year, including key figures of the protest movement. The government made significant efforts to quash the movement and stifle reporting on the protests.
    • In October, 29 leading figures of the protest movement, including members of a committee appointed by the community to represent their grievances to the government, and at least one journalist, were charged under the Anti-Terrorism Proclamation.
    • In both May and October, Voice of America correspondents were temporarily detained and interrogated over interviews they had conducted with protesters.
    The few remaining vestiges of the independent media were subjected to even further restrictions.
    • In April, Temesgen Desalegn, the editor of Feteh, one of the last remaining independent publications, was fined for contempt of court for “biased coverage” of the trial of Eskinder Nega and others. Feteh had published statements from some of the defendants. In August, he was charged with criminal offences for articles he had written or published that were deemed critical of the government, or that called for peaceful protests against government repression. He was released after a few days’ detention and the charges were dropped.
    In May, the authorities issued a directive requiring printing houses to remove any content which could be defined as “illegal” by the government from any publications they printed. The unduly broad provisions of the Anti-Terrorism Proclamation meant that much legitimate content could be deemed illegal.
    • In July, an edition of Feteh was impounded after state authorities objected to one cover story on the Muslim protests and another speculating about the Prime Minister’s health. Subsequently, state-run printer Berhanena Selam refused to print Feteh or Finote Netsanet, the publication of the largest opposition party, Unity for Democracy and Justice. In November, the party announced that the government had imposed a total ban on Finote Netsanet.
    A large number of news, politics and human rights websites were blocked.
    In July, Parliament passed the Telecom Fraud Offences Proclamation, which obstructs the provision and use of various internet and telecommunications technologies.

ሰበር ዜና ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ግንቦት 17\2005 ሰልፍ ወደ ግንቦት 25\2005 ተሸጋግሮ በአዲሳባ ከንቲባ ጽ/ቤት እውቅና ተሰጠው!


Monday, 20 May 2013

ህዝባዊ ውይይት በኖርዌይ May 18,2013


ኖርዌይ ኦስሎና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቅዳሜ በ18.05.13 ህዝባዊ ውይይት አደረጉ። ውይይቱ በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ፤ በእስር ለሚንገላቱና ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ለሚሰቃዩና ለተሰደዱ ወገኖች የህሊና ፀሎት በማድረግ ተጀምሯል። በርካታ ታዳሚዎችም ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን ሰልፍ በመደገፍ ጥቁር ልብስ ለብሰው ተገኝተዋል።

Ethiopians meeting in Norwayውይይቱ የተጠራው በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል ሲሆን ያተኮረውም በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ነበር፤
1. በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ  ፖለቲካ ውስጥ ስለሚጫወተው ሚናና በሀገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲ ስለተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
2. ሰላማዊና ሌሎች የትግል ስልቶች በኢትዮጵያ እና ሰማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ
3. ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመገናኛ ብዙሀን፤ ከሰብአዊና ከዲሞክራሲ መብቶች አንጻር
4. ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታና በሀገር ቤት ስለታቀደው የሰማያዊ ፓርቲ ተቃውሞ ሰልፍ
5. የሀይማኖት ነጻነት በኢትዮጵያና ሰማያያዊ ፓርቲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ  የሚሉት ይገኙበታል።
በነዚህ ወቅታዊና አንገብጋቢ ርዕሶች ላይ ለታዳሚዎች የመወያያ ሃሳቦችንና ገለጻዎችን ያቀረቡት በቅደም ተከተል አቶ አርጋው ያቆብ፤ አቶ ዳንኤል አበበ፤ አቶ ዳባ ጉተማ፤ አቶ ዳሂሎን ያሲን እንዲሁም አቶ ሙሀመድ ሲራጅ ሲሆኑ ዝግጅቱንና ውይይቱን የመሩት ደግሞ አቶ ዳዊት መኮንን ናቸው።
በውይይቱ ላይ በርካታና ዝርዝር ጉዳዮችና ሀሳቦች ተነስተዋል።
በውጪ ሀገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራው) በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ጉልህ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አቶ አርጋው በዝርዝ አቅርበዋል። በሚዲያና በቴክኖሎጂ በመደገፍ አገር ውስጥና ውጪ ካሉ ተቃዋሚ ሀይሎች ጋር የመረጃ ልውውጦችንና ቅስቀሳዎችን በማድረግ፤ ለአለም አቀፍ ድርጅቶች አቤቱታን በማቅረብ፤ ሰላማዊ ሰልፎችን በማድረግ፤ በመዋጮ በቁሳቁስና በሞራል ተቃዋሚ ሀይሎችን በመደገፍ፤ ገዢው አካል አለም አቀፋዊ ድጋፍ እንዳያገኝ በማድረግ፤ በሲቪክ ማህበራት በመደራጀት ወዘተ ዲያስፖራው በኢትዮጵያ ለሚደረገው የዲሞክራሲና የነፃነት ትግል ጉልህና ትልቅ ሚና ሊጫወት እንደሚችል አስረድተዋል። በአንፃሩ ደግሞ በሀገር ጉዳይ ላይ የተሳትፎ ማነስ፤ እኔ ምን አገባኝ የማለት፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ አፍራሽ ዜናዎችን በማሰራጨትና የወያኔን ፖለቲካ በማራገብ፤ የመኖሪያ ፈቃድ ካገኙ በኋላ ከትግሉ በማፈግፈግ፤ ለግል ጥቅም በመገዛት ከወያኔዎች ጋር በመተባበር ወዘተ ዲያስፖራው ትግሉን ሊያዳክመው እንደሚችል አስገንዝበው ይህን በተመለከታ ተቃዋሚ ሀይሎች ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ አሳስበዋል።Ethiopian in the Diaspora, meeting in Norway
በሌላ በኩል ደግሞ የሰላማዊ ትግል ስልቶችን በተመለከተ አቶ ዳንኤል እንዳብራሩት፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰላማዊ ትግል ማታገያ ስልቶች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋና የሆኑት ከሶስት እስከ አምስት የሚጠጉ ስልቶችን ጠቅሰዋል። ከነዚህም መካከል ትብብር መንፈግና ተፅዕኖ መፍጠር ይገኙበታል። በዚህ አጋጣሚ አሁን ያለውን ስርዓት ለመለወጥ ሁለገብ የትግል እንቅስቃሴን መደገፍ ተገቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
አቶ ዳባ ጉተማ በበኩላቸው ስለዜጎች መፈናቀል፤ ገዢው ፓርቲ የሚቀሰቅሳቸው ፀብ አጫሪ ሁኔታዎች፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሰላማዊ መንገድ በሚታገሉ ንፁሀን ዜጎች ላይ ስለሚደርሰው ግድያ፤ አፈና፤ እስር፤ እንግልትና ወከባ፤ በኑሮ ውድነትና በመሳሰሉት በገጠርና በከተማ በህዝቡ ላይ ስለሚደርስ ስቃይ፤ በአሁኑ ወቅት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት የሚሆኑት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን መስዋዕት ለማድረግ የቆረጡ መሆናቸው በአጠቃላይ የፖለቲካ መህዳሩ የሚመች እንዳልሆነ፤ እስከዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ገዢ እንጂ መሪ አግኝቶ እንደማያውቅና ያሁኑ ግን ሲኦል እንደሆነበት በዝርዝርና በተጨባጭ ምሳሌዎች በጣም በርካታ ጉዳዮችን አንስተው ለተወያይ ታዳሚዎች አቅርበዋል። በተጨማሪም ትላንት ካልነበረ ዛሬ እንደሌለ ዛሬ ከሌለ ደግሞ ነገ እንደማይኖር የታወቀ ስለሆነ ለዛሬ በጣም እንድናስብበት አሳስበዋል።
እንዲሁም አቶ ዳሂሎን ያሲን በተለይ በአሁኑ ወቅት ያለውን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታና ሰማያዊ ፓርቲ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍን አቶ ዳሂሎን እንደመነሻ የምርጫ 97 ሰላማዊ ሰልፍን ካነሱ በኋላ በአሁኑ ወቅት በይፋ ስለተጠራው ስለዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ሊኖሩት ስለሚችሉት አሉታዊና አዎንታዊ ገፅታዎች አብራርተዋል። በዋናነትም የሰላማዊ ሰልፉ መጠራት ቢሳካም ባይሳካም ያለውን ጠቀሜታና በንፅፅርም የሚታዩትን ስጋቶች ተንትነዋል።Ethiopians gathered in Norway to discuss current Ethiopian politics
በወቅቱ በኢትዮጵያ ስላለው የሙስሊም ወገኖቻችንን ጥያቄዎችና በገዢ አካል ስለሚደረገው የሀይማኖት መብት ረገጣ በተጨማሪም አሁን ስላለው ችግር መንስኤ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ በአቶ ሙሀመድ ሲራጅ ቀርቧል።
ታዳሚዎችም በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን በማንሳት ከፍተኛ ተሳትፎ የተደረገበት ውይይት አድርገዋል።
በመጨረሻም የወያኔው መሪ መለስ ዜናዊ በጋዜጠኛ አበበ ገላው የተደረገበትን ተቃውሞ አንደኛ አመት በማስታወስ ነፃነት ነፃነት ነፃነት የሚለው መሪ ቃል በህብረት፣ በስብሰባው  መክፈጫ ላይ ተብሎ እንደተጀመረ ሁሉ የእለቱ ስብሰባ  ሲጠናቀቅም  በተመሳሳይ መልኩ ተሰብሳቢዉ  ከመቀመጫቸዉ ተነስተዉ በአንድ ድምፅ ነፃነት! ነፃነት! ነፃነት!  የሚለዉን ቃል አሰምተዋል።
በስብሰባዉ ማጠቃለያ  ተሰብሳቢዉ በጋራ የተስማሙባቸዉን  የሚከተሉትን ሦስት አበይት ሃሳቦች የስብሰባዉ የአቋም መግለጫ በማድረግ የእለቱን ስብሰባ አጠናቀዋል።
1ኛ.በኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት፣የፖለቲካና ሃይማኖት ነፃነት፣ እንዲከበር በተጨማሪ የንፁሃን ወገኖቻችንን ከቤት ንብረታቸዉ አፈናቅለዉ ለሞት ያደረጓቸዉን ሰዋችና የመንግስት ባለስልጣናት፣የሃይማኖት መብት ጥያቄ ባቀረቡ ያሰሯቸዉና የገደሏቸዉን ባለሰልጣናት እነዲሁም በኢትዮጵያ በተለያየ ቦታ የፖለቲካ፣የሚዲያና ሲቪክ ማህበራት አባላትና መሪዋችን ያሰሩና ደም ያፈሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
2ኛ.በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰማያዊ ፓርቲ የጠራዉን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚደግፉ በጋራ አቋም መግለጫቸዉ አረጋግጠዋል።በተጨማሪ ከአገር ዉጪና በአገር ቤት ያሉ የፖለቲካ፣የሲቪክ፣የሐይማኖት፣ የሴቶችና ወጣቶች መህበራት ሰማያዊ ፓርቲ ለጠራዉ ሰልፍ በተመሳሳይ መልኩ ድጋፍ እንዲያርጉላቸዉ ተሰብሳቢዉ አክለዉ በአቋም መግለጫቸዉ አሳዉቀዋል።
3ኛ.በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እያንዳንዳቸዉ የፌስቡካቸዉን ፕሮፋይል በማጥቆርና ቀስቃሽ ድጋፍ ሰጪ ፅሑፎችን ለሌለዉ በማሰራጨት፣እንዲሁም በፓልቶክና በሎሎች ብዙሃን ማሰራጫ ድጋፋቸዉን እንደሚሰጡና ሌላዉም ኢትዮጵያዊ በተመሳሳይ ሁኔታ ድጋፉን በመስጠት ሁሉም የዜግነቱን ግዳጅ እንዲወጣ አሳስበዋል።
አንድነት ሃይል ነዉ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!
በኖርዌይ ለወገን ደራሽ ግብረ ሀይል

Sunday, 19 May 2013

ማን ነው ወንጀለኛው?


በከፍተኛ ደረጃ የህዝብ እምነት ያጣው የካንጋሮው ፍርድቤት ምንም አይነት የህግ ወይም የሞራል የበላይነት ሳይኖረው፤ የህሊና እስረኞቹን የእድሜ ልክና እና ሌሎች ቅጣቶችን እንዴት ሊሰጥ ይችላል? ማነው ፈራጁ? ማንስ ነው ተፈራጁ? ማን ነው ጥፋተኛው። ህግን ያዋረደ? ወይስ ስለነጻነት፣ ስለ ዲሞክራሲ አቤት ያለ?
በፍትህ እና በፍትህ ፈላጊዎች ላይ እየቀለደ እና ተቋሙን እያዋረደ የሚገኘው ወያኔ ዛሬም እንደትላንቱ ሌላ የበደል ጩኸት ከተባዳዮቹ ለበዳዮቹ እንዳይሰማ በጉጅሌ “ዳኞ” ተብየዎች አማካኝነት ውሳኔ ሰጥቷል። እውነተኛ ፍትህ ሀገራችን ውስጥ ጠፍቶ መቀበሩን ለማሳየት ሲል ባስቀመጣቸው የፍትህ ተወናያን ዳኞች አማካኝነት አረፍን እንቀመጥ ዘንድ ፍትህን ትመኙታላችሁ እንጅ አታገኙትም ሲል መልክቱን በአሻንጉሊቶች ፍርድቤቶች አማካኝነት አስተላልፏል።
የገዥው ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ዳኞች ሰሞኑን የሰጡት ፓለቲካዊ ውሳኔ የአገልጋይነታቸውን ታማኝነት ማረጋገጫ እንጅ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ህወሃት እያለ ፍትህና ፍትህ ፈላጊዎችን ማገናኘት የማይታሰብ መሆኑን በድጋሜ ተረጋግጧል፡፡ ፍትህ የነፃነትና የእኩልነት ማረጋገጫ፤ ግለሰቦችና ቡድኖች በሥርዓት እንዲኖሩ ማድረጊያ እና የአንድ ማኅበረሰብ የሞራል እሴቶች ተፈፃሚነት ማሳያ ነበር፡፡ ፍትህ በሌለበት ነፃነት፣ እኩልነት፣ ሰላም፣ ልማት እና ዲሞክራሲ ትርጉም የላቸውም፡፡
ለዚህም ነው ራሱ የፍትህ ስርአቱ ተቋም የካድሬዎች እስረኛ ነው የምንለው። ተቋማት ነጻ አልወጡም፣ ህዝባችን በጎጠኝነት የአገዛዝ አባዜ ይሰቀያል። በማንነቱ ይሰደዳል፣ ይታሰራል። ታዲያ ማን ነው ጥፋተኛው? በዳዩ ወይስ ተበዳዩ?
ዜጎች በሀገራቸው የመኖር፣ የመናገር ፍትህ የማግኘት ተስፋቸው እንደገና ተቀብሯል። ተዋርደናል፤ ውርደት እስከ መቼ? ኢትዮጵያዊ እምቢተኝነታችን፣ ክብርና ኩራታችን፣ ታሪካችን በወያኔዎች ተደፍሯል። በፋሲካ የጀግናው ሰማእታት የአቡነ ጴጥሮስ የመታሰቢያ ሀውልት ለረጅም ጊዜ ከተቀመጠበት፣ ከመታሰቢያነቱ ስፍራ አሻራነቱ ተነስቷል። በዚሁ ዋዜማ እነ አንዷለምአራጌ፣ እስክንድር ነጋ፣ ክንፈሚካኤል ደበበ፣ ናትናኤል መኮነን፣ ምትኩ ዳምጤ፣ ዮሃንስ ተረፈ እና ሻምበል የሺዋስ ይሁን አለም ላይ በፋሲካ ዋዜማ አይሁዶች የህሊና እስረኞቹ ይሰቀሉላቸው ዘንድ ፈረዱ።
በፋሲካ በወያኔ ጨለማ ቤት ውስጥ የተዘጉ፣ የተረሱ ዜጎችም አሉ እነ በቀለ፣ ርእዮት፣ ውብሸት እና እነ ጀኒራል ተፈራ ማሞ እና ሌሎቹም። አሁንም በፋሲካ ህዝቡ እየተሰደደ፣ እየተፈናቀለ ነው። በአንጻሩ አይሁዶች እጃቸውን በደም እየታጠቡ ከደሙ ንጹህ ለመሆን ሲሉ ውስኪ ሲራጩ ይታያሉ። ማን ነው ወንጀለኛው?
ኢህአዴግ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በሾማቸው “ዳኞች” ተብየዎች ስም እያፈራረሳት ነው። ትውልድን የቁም እስረኛና አንገቱን እንዲደፋ እንዲሸማቀቅ እያደረጉት ነው። ሀገራችን በወረበሎች አንገቷን ደፍታ የወያኔዎች መሳለቂያ ሆናለች። እናድናት።
የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ፡ የበደል ትልቅና ትንሽ የለውም። በወያኔ ያልተገረፈ፣ ያልተሰደደ፣ ያልተገደለ፣ ያልታሰረ፣ ያልቆሰለ፣ ሀብት ንብረቱን ያልተወረሰ፣ ያልተዋረደ፣ አንገቱን ያልደፋ፣ ያልተበደለ፣ ፍትህን ያልተነፈገ፣ የእምነት ነጻነቱን ያልተገፈፈ ዜጋ የለም። ያጣነው ብዙ ነው። ያጣነውን የማስመለስ ኢትዮጵያዊ ግዴታ አለብን። ሀገራችን ኢትዮጵያ ይህን ውርደትና መከራ እና አይን ያወጣ ጭካኔ ዘረኝነት ብዝቶና ተባብሶ ህልውናዋ ከመጥፋቱ ዜጎቿ የህሊና እስረኞች ሁነው ፍትህ አጥተው ከማለቃቸው በፊት የሚደርሱላት ጀግኖችን ትሻለች።
ወጣቱ ትውልድ ከገባበት የፍርሃት አረንቋ ወጥቶ፣ ፍርሃቱን በጀግነነቱ በጥሶ ኢትዮጵያንና ወገኑን ለማዳንና ነጻነትን በመሰዋእቱ ከፍሎ ለሀገራችን ብርሃን የመሆኛ ጊዜው አሁን ነው። እምቢ ብለህ የነጻነት ተስፋ የሆኑ ህዝባዊ ሃይሎችን ተቀላቀል። ትግል በአንድ ጀምበር የሚያልቅ አይደለም። በርካታ ረጅምና አስቸጋሪ ፈተናዎች ያሉበት፣ የሚጠበቁበት ነው። ቁም ነገሩ ይህንን የተጋረደብህን ፈተና ተፈትነህ ማለፉ ላይ ነው ጀግንነቱ። እንዲህ አይነት ፈተና አምባገነን መንግስት እሰከ አለ ድረስ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ መከበር በሚነሱ ሃይላት ላይ የሚኖርና የሚቀጥል በመሆኑ፤ በወያኔ በሚደርስብን የስቃይ ውርጅብኝ ሳንበረከክ ለፍትህ ስርአት መከበር ለህግ የበላይነት መስፈን ለሀገር አንድነት የምናደርገውን ትግል በማጠናከር መቀጠልና ግንባር ቀደም ታጋዮች መሆን ይኖርብናል።
ግንቦት 7 የፍትህ የዲሞክራሲና የነጻነት ንቅናቄ ለፍትህ መቆም ሲል ነፃነቱንና ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ሁሉ በማናቸውም መንገድ ወያኔን የመታገል ሞራላዊ ግዴታ አለበት ይላል፡፡ ከትግሉ ባሻገር በነጻነት ታጋዮች ላይ የሀሰት ምስክር የሚሰጡትን፣ ፍትህን የሚየዛቡ ዳኞችና አቃቤዓነ-ህግን የክህደት ሥራዎቻቸውን መዝግቦ መያዝ፣ በዓይነ ቁራኛ መከታተል የሁላችንም ግዴታ ነው፡፡
ህዝብ በሃሰት ምስክሮች፣ ዳኞችና አቃቢያነ-ህግ ላይ ቁጣውን የሚገልጽበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ በወያኔ ወኔ ቢስ አድርባዮች ፍትህ ስትቀበር፣ ዘረኝነት ሲወደስ፣ ታጋዮቻችን ሲገደሉ፣ ሲንገላቱና ሲበደሉ ሲታሰሩ ማየት በቃን ብለናል፡፡ ፍትህን የሚያረክሱትን የወያኔ ቅጠረኞችን በቁርጠኛነት፣ አምርረን እንታገላለን፡፡ የወያኔ ቡችላ ፍርድቤት አገልጋዮች ወዮላችሁ! ያላገጣችሁበት ፍትህ እናንተን ባልጠበቃችሁት ሁኔታ፣ ግዜና ቦታ ትጠየቃችኋለች፡፡ ስለዚህ ራሳችሁን ከቁም እስረኝነትና አገልጋይነት፣ አሽከርነትና ከአደርባይነት ታወጡ ዘንድ ጊዜው አልረፈደባችሁም። እድሉን የመጠቀም ሃላፊነት የእናንተ ነው። እኛ ግን በቃ ብለናል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!
G7 Editor
May 10,2013