Sunday, 17 February 2013

ይህው ነው ሚስጥሩ የመተባበሩ ያአንድነት እድምታው ውብ ስብስቡ

ይህው ነው ሚስጥሩ የመተባበሩ
ያአንድነት እድምታው ውብ ስብስቡ
አላማው አንድ ነው ወገን ከወገኑ
የዋለበቱ ቀን የተጋራው ፍቅሩን

ህብረት በአንድነት ተገልጾ ሲታይ
ቅንነት ሸብቦት በአንድ መደረክ ላይ
ድካም ጉልበት ሲያገኝ ሽንፈት አቅም ሲያጣ
ፍቅር የሞላበት እውነተኛ ደስታ

ትውስታን ይፈጥራል ያንን የድሮውን
የአያቴን ዘመን ታሪክ የሆነውን
አንተ ትብስ አንች የተባባሉትን
ተደጋግፎ ጉዞ የዘለቁበትን
አይዙዋችሁ በርቱ የተባለለትን

በአኩርታችሁናል ወገን ደጋፊነት
ጥሩ ቀን ነበረች ወግን ያየንበት
ተያይዞ ጕዞ በረከት ያለበት
ደስታን የፈጠረ ደስ የተሰኝባት

http://www.ecadforum.com/Amharic/archives/6119