Sunday 12 May 2013

የሰማያዊ ፓረቲ የሰላማዊ ትግል ጥሪ እና የህገመንግስቱ አተገባበር!

ህጉማ ህግ ነበር ፣አተጋገበሩና ተግባሪው ከህጉ ጋር የሰማይ እና የምድር ያህል ተራራቊ እንጂ!

ሰማያዊ ፓርቲ የአፍሪካ ህብረት የተመሰረተበትን 50ኛ አመት የሚከበርበት እለት ግንቦት 17/2005 ምክንያት በማድረግ የፍትህ ጥያቄዎቹን ይዞ ጩህቱን ለማሰማት የሰላማዊ ትግል እና የሰላማዊ ሰልፍ ግብዣውን ለተበደለው ህዝብ ፍቃድ ደግሞ ለመንግስት እያቀረበ ነው።

እንደ ኢትዮጲያ መተዳደሪያ ህገመንግስት ምእራፍ 3 ክፍል 2 አንቀጽ 30 ማንኛውም ግለሰብ በህብረት የመሰብሰብ እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፎችን የማድረግ መብት እንዳለው የሚጠቅስ ሲሆን የኢትዮጲያ መንግስት ግን በየግዜው ግለሰቦችንም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሰላማዊ ትግላቸውን እንዳያካሂዱ ከሆቴል አዳራሽ ጄምሮ በመከልከል ተጽኖ ሲያደደርግ እና ግለሰቦችን ከአሸባሪ ተግባር ጋር በተገናኜ ስያሜ በየጊዜው እንደለቡ ሲያስር ይታያል።


ሆኖም ግን ይህ ተጽኖ ሰማያዊ ፓርቲን ከትግሉ ሳያግደው ዛሬም᎓መንግስት ለፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን የታገሉ ጋዚጠኞችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር አባላት አሸባሪ በማለት በማሰሩ፤ ዜጎች ለአመታት ከኖሩበት መፈናቀላቸውን፤ የመንግስትን የሀይማኖት ጣልቃ ገብነት፤ የኑሮ ውድነትን እንዲሁም በአጠቃላይ በተደጋጋሚው ፓርቲው ጠይቆ ምላሽ ያላገኘበትን የፍትህ ጥያቄዎቹን በመያዝ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ ᎐ም ጀምሮ በአዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል መክንያት በማድረግ የተለያዩ ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች በሚገኙበት ድምጻችንን ለማሰማት ከግንቦት 15 እስከ 17 ቀን 2005 ዓ᎐ም ድረስ ጥቁር ልብስ በመልበስ እና በእለቱ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ᎐ም ደግሞ በአሪካ ጽህፈት ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ እንጠይቃለን ብለዋል። እነዚህ ጥያቄዎች እንዲመለሱ የሚፈልግ የፖለቲካ ፓርቲ᎓ የሲቪክ ማህበራትና ማንናውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሚደረገው የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች በመሳተፍ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ፓርቲው አስታውቋል።


እንደዚህ አይነት የመንግስት አፈና እና ተጽኖ እንዲሁም ኢ ሰብአዊ ድርጊት ባለበት ሁኔታ  በአገር ውስጥ ያሉ የፓለቲካ ተቃዋሚ ድርጂቶች ሰላማዊ ሰልፎችን አይጠሩም ᎓ ተቃውሞአቸውንም ለመግለጽ ድፍረቱ የላቸውም እየተባሉ በተደጋጋሚ ይተቻሉ።
ህግን ተላልፈዋል ፥ህግን አላከበሩም እያለ በሀሰት ክስ ግለሰቦችን እንደልቡ የሚያስረው ይሀው እራሱ መንግስት መተዳደሪያ ብሎ ለያዘው ህግ ተገዥ ላልሆነበት እና የህግ የበላይነት በማይታይበት አገዛዝ ላይ እንዲህ አይነት ጥሪ የእስር ቤቶችን ግንባታ ለመንግት የማስፍፊያ ሌላው መንገድ ይሆንለታል ምክንያቱስ ቢባል እስር ቤቶቹ በጥያቄ አለኝ ብቻ ተብለው በተነሱ ግለሰቦች እና ያለውን እውነት ጋሀድ ባወጡ ጋዜጠኞች ᎓ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር እና አባላት እንዲሁም መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ ገብነት ያቁም በሚል የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ስለተሞላ እና ስለተጣበበ ነው።

መንግስት በህገ መንግስቱ ላይ ያለውን የዜጎች መብት እንዲያው ለአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ለፕሮፓጋንዳነት ልጠቀምበት እና አንድ ገዜ እንኩዋን ልፍቀድ ብሎ  ቢፈቅድ እንኩዋን በእለቱ ለሰላማዊ ትግል የወጡትን ዜጎች በአሸባሪነት ላለማሰሩ ዋስትና የለም። ያው በእለቱ ለሚጠየቊት የፍትህ ጥያቄዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ማለቱ የማይቀር እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

ይህም ሆኖ ያለ ትግል እና ያለመስዋት ነጻነትን እና ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ማምጣት የማይሆን ስለሆነ ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የተጽእኖ ገደብ አልፎ በመውጣት የሰላማዊ  ትግል ጥሪውን ማቅረብ ችሏል።


No comments:

Post a Comment