ሐሙስ, ኤፕረል 18, 2013 VOA
በምዕራብ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚኖሩ የአማራ ብሄር አባል የሆኑ አርሦ አደሮች «ለዓመታት ከኖርንበት እየተፈናቀልን ነው፤ መድረሻ ግን የለንም» ሲሉ አቤቱታ እያሰሙ ነው፡፡
ይህንኑ ቅሬታቸውን መነሻ በማድረግ ሁለት አርሦ አደሮችን ባለፈው የካቲት 29, 2005 ዓ.ም መዘገባችን ይታወሳል።
በማግስቱ መጋቢት 30 / 2005 ዓ.ም መልስ የሰጡን የክልሉ ፕሬዚደንት ግን ማንም በግድ እንዳልተባረረ በማስተባበል የሠፈሩበት ቦታ ለቤቶች ግንባታ ስለሚፈለግ በምትኩ ሌላ የእርሻ ማሳ ተስጥቷቸዋል ማለታቸውንም ዘግበናል።
ከየትና ከመቼ ጀምሮ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ቀበሌዎች የአማራ ገበሬዎች መፈናቀል እንደጀመሩ ምክንያቱን ጭምር አንድ ተፈናቃይ ገልፀውልናል፤ የበቀል እርምጃ እንዳይወሰድባቸው በመሥጋት ግን ስማቸው እንዳይገለፅ ጠይቀዋል።
No comments:
Post a Comment