Thursday 25 July 2013

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ባለቤት ሰርካለም ፋሲል ከአገር ወጣች

ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በትላንትናው እለት ከኢትዮጵያ መውጣቷ ታወቀ። ጋዜጠኛ ሰርካለም በ1997ቱ ግርግር ወቅት፤ ከቅንጅት መሪዎች እና ሌሎች የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ጋር በእስር የቆየች ሲሆን፤ ወንድ ልጇን ናፍቆት እስክንድርን የወለደችውም በቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ በነበረችበት ወቅት መሆኑ ይታወሳል።
Eskinder, serkalem and Nafekot
Eskinder and Serkalem with their son Nafekot, right after they released from Kaliti prison in 2007,
አሁን ሰርካለም ፋሲል በተለይ ከአገር ለመውጣት የተገደደችው በባለቤቷ እስክንድር ነጋ ላይ በደረሰበት ህገ ወጥ እስር ሲሆን፤ በተለይም ከዚህ በኋላ ልጃቸው ወደ አሜሪካ መጥቶ እንዲማር በመወሰናቸው ጭምር ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት  በኢ.ኤም.ኤፍ. ባቀረብነው ዘገባ ላይ እስክንድርን በቃሊቲ ያነጋገረችው ተባባሪያችን የእስክንድርን ነጋን ቃል እንዲህ በማለት ነበር የገለጸችው። “በ እስር ላይ ባለሁበት ባሁኑ ወቅት እጅግ አስቸጋሪ እና አስጨናቂ የሆነብኝ፤ የልጄ እና የባለቤቴ ጉዳይ ነበር። አሁን ግን ከአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ስላገኙ፤ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሰርካለም እና ልጄ ወደ አሜሪካ ይሄዳሉ። የነሱ ወደዚያ መሄድ ለኔ ትልቅ የህሊና እረፍት ይሰጠኛል።” ብሎ ነበር።
በዚህም መሰረት ሰርካለም ፋሲል የውጭውን አለም ስትቀላቀል፤ 132ኛ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ትሆናለች ማለት ነው።

http://ethioforum.org/%E1%8B%A8%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A0%E1%8A%9B-%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%8A%AD%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%88%AD-%E1%8A%90%E1%8C%8B-%E1%89%A3%E1%88%88%E1%89%A4%E1%89%B5-%E1%88%B0%E1%88%AD%E1%8A%AB%E1%88%88/

No comments:

Post a Comment