Saturday 20 April 2013

ዜና ገራሚ፤ ቤኒሻንጉል ክልል የሄዱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ!


77133_405796946184925_1236718947_n
ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል “ውጡ” ተብለው ከተባረሩ በኋላ ደግሞ “ግቡ” ተብለው የተመለሱ ወገኖች ያሉበትን ሁኔታ ለማየት የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት ሚያዝያ 11/2005 ዓ.ም ወደ ክልሉ አምርተው ነበር፡፡ መተከል ዞን ሲደርሱ ግን የዞኑ ፖሊስ አስሯቸዋል፡፡
የዞኑ ፖሊስን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት የለም፡፡ እንደምንገምተው ግን ፖሊስ፤ የፓርቲው አመራር አባላትን ሲመለከት፤ የውጪ ሀገር ሰዎች ህገ ወጥ ዝውውር ሲያደርጉ የያዛቸው መስሎት ሳይሆን እንደማይቀር ይጠረጠራል!
ጎበዝ፤ ሀገር ቤት ዘመዶቻችንንም ለማየት ልንከለከል ነው ማለት ነው…!?
በሳውዲ፣ በየመን፣ በኬኒያ በታንዛኒያ ህገ ወጥ ዝውውር አደረጋችሁ ተብለን ለምንታሰረው ስለምን እንገረማለን እነሆ በራሳችን ሀገር ከክልል ክልል መዘዋወርስ መቼ ተቻለን…!?

By Abe Tokichaw

No comments:

Post a Comment